በወሎ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመው የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ማዕከል ተመረቀ። =======================
  May 12, 2020    News

የኮሮና ቫይረሱ በሀገራችን ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ቫይረሱን ለመከላከል የኮምቦልቻና የደሴ ግቢዎችን የማግለያ ማዕከል በማድረግ እየተጠባበቀ ያለው የወሎ ዩኒቨርሲቲ የምርመራ ማሽኖችን በተቋሙ በማስገባት አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው የተቋሙና የአማራ ክልል ባለስልጣናት በተገኙበት የምርመራ ማዕከሉን በማስመረቅ ለስራ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። ይህ የምርመራ ማእከል በምስራቅ አማራ ዋነኛ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ሁኖ የሚያገለግል ሲሆን ቫይረሱ የሚገኝባቸው አካላት ካሉ በቦሩ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት እንድያገኙ በማድረግ ተናቦ የሚሰራ ይሆናል። ዩኒቨርሲቲው ከ802 በላይ አልጋዎችን በማዘጋጀት ተቋሙ የማግለያና የምርመራ ማዕከል ሁኖ እንድሰራ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል። The Coronation Center that was established in wollo university has been elected. ======================= Since the time of coro and virus has been appointed to protect the virus in our country since it happened in our country, it has been appointed to protect the virus and dessie areas. The University has announced that it is ready to work with amhara region officials. This election center will serve as a main research in east amhara and virus, and it will work to get medical service in the hospital hospital. The University has finished the preparation to work as a center of the institution that has prepared more than 802 beds.