ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከ3ሺ 5 መቶ በላይ ተማሪዎች አስመረቀ።
  July 15, 2019    News

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለ11 ጊዜ በደሴና በኮምቦልቻ ግቢዎች ያሰለጠናቸውን 3525 ተማሪዎች አስመርቋል። ከነዚህ ተመራቂዎች መካከል 913ቱ በኮምቦልቻ የተመረቁ ሲሆን በአጠቃላይ በ2011 ዓ ም በመደበኛ በርቀትና ተከታታይ ፕሮግራሞች 6538 ተማሪዎችን አስመርቋል። በዚህ የምርቃት ፕሮግራም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትርን ጨምሮ በርካታ የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል። ከምርቃት በኋላ የዕለቱ የክብር እንግዶች፡ ጥሪ የተደረገላቸው ግለሰቦችና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በጢጣ ወሎ ቴርሸሪ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄደዋል።