በኮምቦልቻ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በተመራቂ ተማሪዎች የተሰሩ የፈጠራ ውጤቶች ለእይታ ቀረቡ።
  July 11, 2019    News

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የተማሪዎች ምርቃት ፕሮግራም ላይ ለእይታ የቀረቡት የተመራቂ ተማሪዎች የፈጠራ ውጤቶች ተቋሙ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ በገሀድ አሳይቷል። በዚህ የተማሪዎች ምርቃት ላይ በሶስት የሜካኒካል ምህድስና ተመራቂ ተማሪዎች ተሰርቶ በመሬት ላይ እየተሽከረከረ የታየው አውሮፕላን የብዙሀኑን ስሜት በመሳብ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ተነግሮለታል። በኮምቦልቻ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በምህንድስናና በኮምፒዩተር ሳይንስ የሞያ ዘርፎች 913 ተማሪዎች ተመርቃዋል።