ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ60 ሺ ብር ወጭ እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በመግዛት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አርሶ አደሮች አሰራጨ።
  July 11, 2019    News

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በደሴ ዙሪያ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 200 ሴቶች 400 እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በመግዛት አሰራጭቷል። ዩኒቨርሲቲው የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ለዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሴቶች ያሰራጨው በህጻናት ላይ የሚደርሰውን የአካል መቀንጨር ለመከላከል ነው።