ወሎ ዩኒቨርስቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2012 እና የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምርጫን በonline ኤሌክትሮኒክስ አካሄደ።
  July 11, 2019    News

ወሎ ዩኒቨርስቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2012 እና የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምርጫን በonline ኤሌክትሮኒክስ አካሄደ። ከ160 በላይ ተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ የድምፅ ብልጫ ያገኙ 12 ተወዳዳሪዎችን የስራ አስፈጻሚ ሆነው ተመርጠዋል። ኢንስቲትዩቱ የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴዎችን በማዋቀር በonline የኤሌክትሮኒክስ ምርጫን ግልጽነትና ተአማኒነት ያለውን ምርጫ በሰላማዊ መንገድ አካሂዷል። የኢንስቲትዩት ተማሪዎችም የምርጫውን ሂደት በቀጥታ በአውትዶር ስክሪን በመከታተል ግልጽ የሆነ ስኬታማ የኤሌክትሮኒክስ ምርጫው በመካሄዱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። በምርጫ ተወዳድራችሁ በአብላጫ ድምጽ ላሸነፋችሁ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች መልካም የስራ እና የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ ወሎ ዩኒቨርሲቲ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።