የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከደሴ ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያና ከኢትዮጵያ ቤተ መዘክርና መዛግብት ጋር በመተባበር የንባብ ሳምንት በደሴ ከተማ እያካሄደ ነው።
  February 17, 2019    News

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከደሴ ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያና ከኢትዮጵያ ቤተ መዘክርና መዛግብት ጋር በመተባበር የንባብ ሳምንት በደሴ ከተማ እያካሄደ ነው። የታዳጊዎችን የንባብ ልምድ ለማጎልበት ከታህሳስ 24-26/2011 ዓ ም በደሴ ከተማ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የንባብ ቀን ዛሬ በተለያዩ ዝግጅቶች ተጀምሯል። በዚህም ፕሮግራም በመታደም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደሴ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ም/ሀላፊ አቶ ተስፋየ ጫኔ የሰው ልጅ ለመኖር ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ አእምሮም በምክንያታዊነት ነገሮችን ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም ዘወትን አንባቢ መሆን ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል። በፕሮግራሙም የግጥም ውድድሮች፥ የንባብ ክህሎት ለማሳደግ ወጣቶች መከተል የሚገባቸው አስተምሮዎችና የታዋቂ ደርሲ ንግግሮች ተደርገዋል። ፕሮግራሙም እስከ ታህሳስ 26/2011 ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በማጠቃለያው ፕሮግራም የድምጽ ተሰጥኦ ያላቸው ውድድሮችን በማካሄድ ታዋቂ የጥበብ ባለሞያዎች የደሴንና አካባቢዋን አርት ለማሳደግ የሚያስችል የመማማሪያ መድረክ እንደሚኖር ይጠበቃል።