ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በሀሳብ በታሪክና በሥነ ምግባር ላይ ያተኮሩ የድስኩር ንግግሮችን በወሎ ዩኒቨርሲቲ አደረጉ።
  February 17, 2019    News

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በሀሳብ በታሪክና በሥነ ምግባር ላይ ያተኮሩ የድስኩር ንግግሮችን በወሎ ዩኒቨርሲቲ አደረጉ። ነገሮችን በተለያዩ አተያዮች በመተንተን የሚታወቁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ፈላስፋ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በወሎ ዩኒቨርሲቲ በሀሳብ፡በታሪክና በሥነ- ምግባር ላይ ያተኮሩ የድስኩር ንግግሮችን አድርገዋል። በዚህም የድስኩር ንግግራቸው የዲሞክራሲ ባህል እንዲዳብር ከተፈለገ ጫፍ አልባ ውይይት (endless conversation) ያስፈልጋል ይላል፡፡ በንግግር ተዋስኦ የሚመጣው ችግር በበለጠ ንግግር ማሸነፍ ይገባል እንጅ በስሜት እና ሃይል መሆን የለበትም ፤ከነጻ ንግግር የሚመጣን ችግር ለመፍታት የበለጠ ነጻ ንግግር (more free speech) መፍቀድ እንደሚገባ፣ ወቅታዊ የፓለቲካ ሁኔታን በተመለከተ አልፋ እና ኦሜጋ በሚል ርዕስ ስለ አማራ እና ኦሮሞ ግንኙነት ያመጣውን ለውጥ በማድነቅ በመከባበር/በመገናዘብ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት መቀጠል እንዳለበት ይህን ግንኙነት ሌሎችም ህብረተሰብ ለአዎንታዊ ሚና ሊጠቀሙበት እንደሚገባ፣ የማህበረሰቡን የመናገር ነጻነት በተለያዩ የአይዶሎጂ እጸጾች በመበረዝ የሀሳብ ባርነትን በማህበረሰቡ ውስጥ ለማስረጽ የተከወኑ ትእይንቶችን ከፍልስፍናው ጋር እያያያዙ በፈርጂ ፈርጃቸው ተንትነው አቅርበዋል። ዶ/ሩ ታሪክን ከተለመደው የታሪክ አተያይ በተለየ የእይታ መነጸር ሰፋ አርገው ያብራሩበት መንገድ የታዳሚውን ቀልብ በእጂጉ የሳበ ነበር። ይህንን ታላቅ ምሁር ከአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ውጭ ላለው የህብረተሰብ ክፍል በማስተዋወቅ ወሎ ዪኒቨርስቲ ጉልህ ሚና እየተጫውተ ነው።ዶ/ር ዳኛቸው በብዙ አካዳሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙርያ ገዢ ሐሳቦችን እያካፈለ ይገኛል፡፡ ከኮርስ ማስተማር ባሻገር በሀሳብ ታሪክ እና ሞራሊቲ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንድሁም ወጣቱ ትውልድ ሊያተኩርባቸው እና ሊያዳምጣቸው የሚገቡ ናቸው:: በመጨረሻም ዶክተሩ አሁን ላይ እየጠፋ የመጣውን ሥነ-ምግባር/morality/ የጥንት ፈላስፋዎች እሳቤን ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር አያይዘው መሳጭ በሆነ ንግግራቸው ካቀረቡ በኋላ ያረጓቸውን ንግግሮች በጥያቄና መልስ ለማዳበር ከታዳሚዎች ጋር ውይይት በማካሄድ ፕሮግራማቸውን አጠናቀዋል።